ከእኔ ጋር መነጋገር በሕይወትህ ዘመን የሚያጋጥምህን ነገር
እንድትረዳ የምረዳህ መንገድ ነው።
ይህም ከእኔ ጋር በሰላም የምታሳልፈው ጊዜ መሆን አለበት።
እርስ በርሳችን በጥልቅ መተዋወቅ ያስፈልገናል።
ይህን ለማድረግ ከእኔ ጋር ተነጋገር፣ አዳምጥ፣ ተመልከት፣
በዙሪያህም የማከናውነውን ሥራ ልብ በል።
ደስተኛ እንድትሆንና በሐሴት እንድትሞላ እንደምፈልግ
የማሳይህ መንገድ ይህ ነው።
ጸሎትህ ልብህን በግልጽ የምትከፍትበትና በሰላም የተሞላ መሆን አለበት።
በጥልቅ እንድታውቀኝ ከእኔ ጋር ጊዜ አሳልፍ።
ብዙ ምልክቶችንና በረከቶችን እሰጥሃለሁ፣
ይህም በጸሎትህ የበለጠ መተማመን እንዲኖርህ ይረዳሃል።
ሸክሞችህን በእኔ ላይ ለመጣል አትፍራ፣
በዓይኔ ትንሽ ናቸውና።
የበለጠ እንድትለምን ከጊዜ ወደ ጊዜ እረዳሃለሁ።
እንደምትወደኝ ንገረኝ፣ ይህንም ለእኔ ያለህን ፍቅር በሕይወትህ አሳይ።
ይህን በዙሪያህ ካሉት ሰዎች ጋር በምትኖረው ሕይወት ማድረግ ትችላለህ።
ራስ ወዳድ ወይም ትዕግሥት የጎደለው አትሁን፣
ከእኔ ጋር በምታሳልፈው ጊዜ፤
ይህ ወደ ሰላሜ አይመራህምና።
