ያለህ ይህ ጊዜ ከእኔ የተሰጠህ ስጦታ ነው።
በታላቅ ጥንቃቄ ተጠቀምበት፣
እኔ በምወስነው ጊዜ ያበቃልና።
የሌሎችን ፍላጎት ለማሟላት በዚህ ስጦታ ተጠቀም።
በስጦታዎቻቸው እንዲደሰቱ እርዳቸው፣
እኔም ለአንተ እንደማደርገው።
ስጦታዎችህን ከእኔ ዘንድ እንድትፈልግ እመኛለሁ።
የተትረፈረፈ ደስታ እንድታመጣ እመኛለሁ፣
በዙሪያህ ላሉት።
ከዚህ የሚበልጥ ምን ዓይነት ልግስና ሊገኝ ይችላል?
ከምታገኛቸው ሰዎች ጋር ሰላምን አምጣ።
ደስታና ሰላም ስጣቸው።
በሥቃይ ላይ ላሉት ሕይወትን አምጣ።
ይህን የሥቃይ ጊዜ እንዲያልፉ እርዳቸው።
ባሉበት ሁኔታ ለተቆጡት የዋህ ሁን።
በመንገድህ ሲያጋጥሙህ ጥበብን አምጣላቸው።
ርኅራኄ ከዓይኖችህ ይንጸባረቅ፣
ወደ ሥቃያቸውም ዘልቆ ይግባ።
ብርታትህ ሥቃያቸውን ይፈውሳል።
እንዲፈወሱ ወደ አንተ አመጣቸዋለሁ።
ብርታቴ ወደ እነርሱ እንዲተላለፍ ፍቀድ።
እነዚህ ሰዎች ብርታቴን ይፈልጋሉ።
ለዚህ ዓላማ በአንተ እንድሠራ ፍቀድልኝ።
