ምን ብርሃን ታያለህ
የማታውቃቸውን መልሶች ስትፈልግ?
መልሶችህ ያንሳሉን
ለማወቅ ካለህ ፍላጎት?
ግራ ተጋብተሃልን
በማመዛዘንህና በእረፍት ማጣትህ?
በመጀመሪያ አለመቻልህን እወቅ
ለሕይወት ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት።
ጥቂት ብቻ እንደሚጠበቅብህ
ተረዳ።
ከባድ ሸክም ተሸክመህ ከሆነ፣
እንግዲያው አውርደው።
ከፍ በል፣
ብርሃኔን ስታውቅ።
በሙቀቱና በቸርነቱ ተደሰት።
በአንተ ላይ በሚያሳድረው ስሜት ተበረታታ።
ብርሃኔ እንዲሞላህ ፍቀድ
አንተ በማታውቀው ነገር።
ይህን ፍቀድ።
ይህን ለምን።
ይህን ጠብቅ።
ይህን ገጽ ያጋሩ፦
