መልሶችን ትፈልጋለህ፣ ጥያቄዎችንም ታገኛለህ።
መልስ የሌላቸውን ጥያቄዎች ታገኛለህ።
ምን ዓይነት መልሶች ያስደስቱህ ይሆን?
እምነትህ በእነዚህ ግራ አጋቢ ጉዳዮች ይፈተናል።
እውነትን የማግኘት ፍለጋህ ይሰፋል፣
በእነዚህ ተሞክሮዎች አማካይነት።
እነዚህን ግራ አጋቢ ጉዳዮች እንዴት ትይዛቸዋለህ?
ሰላምን ለማግኘት የምታደርገው ፍለጋ ይምራህ፣
በእኔ ውስጥ መጽናናትን እንድታገኝ።
መልስህ እኔ ነኝ።
እኔን ጠይቀኝ፤
መልሶችህን ለማግኘት ወደ እኔ ተመልከት።
መፍትሔዎችን ማወቅ አያስፈልግህም፣
በሕይወትህ ለሚከሰቱት ነገሮች ሁሉ፤
ይህ ወደ ባሕርዬ ያስገባህ ነበርና።
እንደ ሰው ያሉብህን ውስንነቶች እወቅ፣ እመንም፣
ከእውቀትህ በላይ የሆነው ሁሉ አካል እንደሆንሁ።
ለእኔ ስትገዛ እምነትህ ይጠነክራል።
የምትፈልገውን በእኔ ውስጥ አግኝ፤
ያለው ሁሉ እኔ ነኝ።
የምትፈልገውን ሰላም በእኔ ውስጥ አግኝ፣
የሚያስፈልግህን እሰጥሃለሁና።
ማንነትህን በእኔ ውስጥ አግኝ፣
የፈለግኸው እኔ ነኝና።
ልትረዳው የማትችለው እኔ ነኝ።
