
አፍቃሪና መሐሪ የሆንክ አባታችን እግዚአብሔር ሆይ፣ ቤተሰቦችን ሁሉ በፍቅርና በመረዳዳት ፍጹም አንድነት ሰብስበህ ጠብቃቸው።
በእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ውስጥ እርስ በርስ የመግባባትና የመዋደድ መንፈስን አስርጽ።
ጠብንና ቂምን ከእነርሱ አርቅ፤ አልፎ አልፎ ለሚፈጽሟቸውም ስህተቶች ይቅር ባይነትንና ሰላምን በልባቸው አስፍን።
ወላጆች እርስ በርሳቸው ያላቸው ፍቅርና መዋደድ መልካም ምሳሌ ይሁን።
ልጆች ሌሎችን እንዲያከብሩና በብስለት ራሳቸውን የሚችሉ ሆነው እንዲያድጉ፣ ራሳቸውን የማክበር መንፈስን በውስጣቸው አስርጽ።
በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት፣ ቤተሰቦች እርስ በርሳቸው ያላቸው መዋደድና መከባበር በዚህ ዓለምና በመጪው ሕይወት የክርስቲያናዊ ሕይወት ምልክት ይሁን።
አሜን።