አማርኛ

ለንጉሡ ክርስቶስ የሚቀርብ ጸሎት

ጌታ አምላካችን ሆይ፣ ከሁሉ ይልቅ ቅዱስ የሆንከው ንጉሥና የሕዝቦች ሁሉ ገዥ አንተ ብቻ ነህ።

ጌታ ሆይ፣ አምላካዊ ንጉሥ ሆይ፣ ከአንተ ምሕረትን፣ ሰላምን፣ ፍትሕንና መልካም ነገርን ሁሉ እንደምንቀበል በታላቅ ተስፋ እየጠበቅን ወደ አንተ እንጸልያለን።

ጌታችንና ንጉሣችን ሆይ፣ ቤተሰቦቻችንንና የተወለድንባትን ምድር ጠብቅ።

እጅግ ታማኝ የሆንክ ሆይ፣ እንድትጠብቀን እንለምንሃለን።

ከጠላቶቻችንና ከጽድቅ ፍርድህ ጠብቀን።

ሉዓላዊ ንጉሥ ሆይ፣ በአንተ ላይ የሠራናቸውን ኃጢአቶቻችንን ይቅር በለን።

ኢየሱስ ሆይ፣ አንተ የምሕረት ንጉሥ ነህ።

የጽድቅ ፍርድህ ይገባናል

ጌታ ሆይ፣ ማረን፣ ይቅርም በለን።

በታላቅ ምሕረትህ እንታመናለን።

እጅግ ግርማ ሞገስ ያለህ ንጉሥ ሆይ፣ በፊትህ እንሰግዳለን፣ እንጸልያለንም፤

ንግሥናህ፣ መንግሥትህ፣ በምድር ላይ እውቅና ያግኝ።

አሜን።


ተጨማሪ ጸሎቶች

ዕለታዊ ማሰላሰያዎች