ከምትወዷቸው ጋር አብራችሁ ስትሆኑ፣
ደስ ይለኛል።
ይህን ጊዜ እኔን ለማመስገንና እርስ በርሳችሁ ለመመሰጋገን ተጠቀሙበት።
እያንዳንዳችሁ በሰላም እንድትኖሩ እፈልጋለሁ፣
ከሁሉ ይበልጥ ቅርብ ከሆኗችሁ ሰዎች ጋር።
ይህ ሰላም እናንተ ከምታስቡት በላይ ነው፣
ሁኔታውን ስታዛምዱት
ከሰውኛ ግንዛቤያችሁና ከግንኙነቶቻችሁ ጋር።
ሰላሜ ከእይታችሁ፣ ከምትጠብቁት፣
እና ከግንዛቤያችሁ በላይ ነው።
የምሰጣችሁ ሰላም ሙሉ ነው፤ ግማሽ አይደለም።
የምሰጣችሁ ሰላም ብርሃን ነው፤ ጨለማ አይደለም።
የምሰጣችሁ ሰላም የእኔ ነው፤ የእናንተ አይደለም።
የምሰጣችሁን ተቀበሉ፣
ይህም ስጦታ ከሁሉ ይበልጥ ቅርብ ለሆኗችሁ ሰዎች ይሁን።
ለምን እንደተባረካችሁ መረዳት አያስፈልጋችሁም።
ሰላሜን ይዛችሁ ሂዱ፤ ለሌሎችም ጥቅም አውሉት።
ሰላሜ ይለውጣችኋል፤ ያበረታችኋልም።
ሰላሜ ወደ እኔ ያቀርባችኋል።
ይህን ለምኑ።
አትፍሩ፣
በእናንተ ውስጥ ሊታይ የሚችለውን ለውጥ።
አትፍሩ፣
ይህን ሰላም አብራችኋቸው ላላችሁ ሰዎች ለማካፈል።
ለዚህ ዓላማ በእናንተ ልሠራ እፈልጋለሁ።
በውስጣችሁ እንድኖር ፍቀዱልኝ።
ቃላችሁ ቃሌ ይሁን።
ቃሎቼ ከእናንተ ወደ መስማት ወደሚያስፈልጋቸው ይፈስሳሉ።
በእናንተ እንድሠራ ፍቀዱልኝ። እንድባርካችሁ ፍቀዱልኝ።
