ተመልከትና ዕቅዴን እይ።
አዳምጥና መመሪያዬን ስማ።
እንዴት እንደምቆጣጠር ተመልከትና ተረዳ።
በእኔ መገኘት ተደሰት፣ መገኘቴንም ተቀበል።
ከዚህ የሚበልጥ ምን ደስታ ልትፈልግ ትችላለህ?
ከዚህ የሚበልጥ ምን እርካታ ሊገኝ ይችላል?
ይበልጥ ፍሬያማ የሆነ ሰላም ምንድን ነው?
ይበልጥ እውነተኛ የሆነ ግብ ምንድን ነው?
እውነቴን ፈልግና አግኝ።
ላንተ ያለኝን ዕቅድ ፈልግና እወቅ።
ላንተ ባዘጋጀሁት ሰላሜ ተደሰት።
ሌላ ማንኛውም ነገር እርካታ አያመጣልህም።
ይህን ገጽ ያጋሩ፦
