አማርኛ

አቅጣጫ

የዓለምን መንገዶች ስታስብ፣
  የምታስተምርህንና እንዴት እንደምትፈተን ስትመለከት፣
  ትምህርቴና ፈቃዴ ከዚህ የተለዩ መሆናቸውን እወቅ።

መንገድ ሰጥቼሃለሁ፤
  ከለመንኸኝም፣ ይህን መንገድ ለመከተል
  የሚያስፈልግህን ጸጋ እሰጥሃለሁ።
አላስገድድህም።

በሌሎች በኩል የምሰጥህን ቃላት
  ለማሰብ ዝግጁ ሁን።

ወጥ የሆነ አካሄድ ታያለህ፤
  በጥበብህም
  መንገዴን ትከተላለህ።
ይህም ወደ እኔ ይመራሃል።

በቃላቴና በመመሪያዬ
  እመራሃለሁ።
ይህንን ከእኔ የሆነ ስጦታ አድርጌ
  እሰጥሃለሁ።

የትኛውን መንገድ እንደምትከተል አሳይሃለሁ፤
  ምክንያቱም እንድትከተለው የምፈልገው መንገድ የትኛው እንደሆነ
  ሁልጊዜ በግልጽ ለመለየት አትችልም።
መመሪያዬን ስትለምን
  ይህንን አደርግልሃለሁ።

ለመከተል ልትመርጣቸው የምትችል
  ብዙ አቅጣጫዎች አሉ።
ለአንተ ያለኝን ዕቅድ ለመፈጸም
  የሚያስፈልጉህን
  ስጦታዎች እሰጥሃለሁ።

ልጄ ሁን፤
  ለማካፈል የምጓጓላቸውን ስጦታዎች ለሚፈልጉ ሰዎች
  ሰላምና ደስታ እንድሰጥ እርዳኝ።
ይህንን ለእኔ ስታደርግ፣
  ስለ ሰው ሕልሞች በሚነግሩ
  ግጥሞችና ጽሑፎች ከሚገለጸው የተለየ
  ሰላምና እርካታ ታገኛለህ።
ሰላሜ ወደፊት የሚጠብቅህን እንድትረዳ ያስችልሃል።

ቀጣዩ መንፈሳዊ ማሰላሰያ

ማውጫ