አማርኛ

ዛሬ ከእኔ ጋር ትሆናለህ

በቀኝህ ተሰቅዬ ሳለሁ፣
እያንዳንዱን ቃልህን በጥሞና አዳመጥሁ።
ምላስህ ከመንጋጋህ ጋር ተጣብቆም፣
አሁንም ድምፅህን ሰማሁ።

ለእነርሱ ይቅርታን ለመንህ፣
ምንም ማመካኛ ሳታስቀር።
ትሑትና የዋህ ልብህም፣
ለስድብ ምላሽ አልሰጠም።

ያን ጊዜም እንዲህ ብዬ አሰብሁ፦
“እኔስ ይቅርታን ብለምን?”
ነገር ግን ወንጀሎቼን ሁሉ ማስታወሴ፣
ለመናገር ትንፋሽ አሳጣኝ።

ያን ሁሉ ካደረግሁ በኋላም፣
እጆችህን ዘርግተህ ተቀበልኸኝ።
በምሕረትም እንዲህ ብለህ ጠየቅኸኝ፦
“አሁንም ከእኔ ትሸሻለህ?

“በሕመምህ ከአንተ ጋር ተሠቃይቼ፣
መስቀልህን ተሸክሜ፣
ፍቅርህን ፈልጌ ባጣሁ ጊዜ፣
ያን ጊዜ አንተን በማጣቴ አዘንሁ።

“አሁን ስሕተትህን ለማካካስ፣
ለእኔ ልታቀርብ የምትችለው፣
የዛሬውን ታማኝነትህን ነው፣
እኛም ወዳጆች እንሆናለን።”

“ኢየሱስ ሆይ፣ እባክህ አስታውሰኝ!”
ከጥልቅ እጮኻለሁ።
“ዛሬ ከእኔ ጋር ትሆናለህ፣
ከእንግዲህም ከቶ አትሞትም።”

-አባ ቲሞቲ ጄ. ድሬፐር

ተጨማሪ ግጥሞች

የሕማማት ሳምንትና የፋሲካ ጸሎቶች