ከተስፋ መቁረጥ ራስህን ጠብቅ፣
ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ ይመራሃልና።
ይልቁንም በተስፋ
እና መልካም ነገርን በመጠባበቅ ተከበብ።
ተስፋ የሚያስቆርጥ አስተሳሰብ እንዲከብብህ አትፍቀድ።
በቁጥጥሩ ሥር ከሆንህ፣
ገፍትረህ አስወግደው፤ ራስህንም
በሚጠብቅህ ጸጋዬ ትጥቅ ሸፍን።
የዚህን ጠባቂ ጸጋ ኃይል ልበስ።
ጠላትህን ስትጋፈጥ ይህን ትጥቅ ልበስ።
ስትጎዳ፣
ጸጋዬ ቁስሎችህን እንዲፈውስ ፍቀድ።
ይህ ጥበቃ የአንተ አካል እንዲሆን ፍቀድ፣
ምንም ፍርሃትም አይውጥህም።
ልታሸንፈው ከምትችለው በላይ የሆነ እንቅፋት የለም።
ምንም ሽንፈት አይከብብህም።
በጥበቃዬ አዲስ ጀግንነት እንዲኖርህ ተበረታታ፣
ምንም ጉዳት ሊያጠፋህ አይችልምና።
ጥበቃዬ መንፈስህን እንዲያነቃቃ
ከጸጋዬም ጋር ፊት ለፊት እንዲያገናኝህ ፍቀድ።
