አማርኛ

ቤተ መቅደሱን ማንጻት

የቅዱስ ሰዓት አምልኮ አቀራረብ

የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዮሐንስ 2:13–25

ዐውድ፦ ከላይ ያለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ቢያንስ አንድ ጊዜ ካነበቡ በኋላ፣ ስለ ቤተ መቅደሱ መንጻት አጭር ሆኖም ዝርዝር ትምህርት የሚሰጡትን የሚከተሉትን ነጥቦች ያንብቡ፦

  • የፋሲካ በዓል በየዓመቱ ከሚከበሩት በዓላት ሁሉ ዋነኛው ነበር። ወንዶች ሁሉ በጌታ ፊት መቅረብ ይጠበቅባቸው ነበር። ብዙዎች ይህን የሚፈጽሙት ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ቤተ መቅደሱ በመሄድ ነበር።
  • ሀብታሞች በጎችን ወይም በሬዎችን ያቀርቡ ነበር። ድሆች ደግሞ ዋኖስ ወይም ርግብ ያቀርቡ ነበር።
  • በበዓሉ ምክንያት ቤተ መቅደሱ በሰዎች ተጨናንቆ ነበር። ከእነርሱም ብዙዎቹ፣ ሰዎች በጌታ ፊት የመቅረብና መሥዋዕት የማቅረብ ሃይማኖታዊ ግዴታ እንዳለባቸው ተጠቅመው ገንዘብ ለማግኘት ይሞክሩ ነበር።
  • ቅዱስ ኢግናጥዮስ እንደሚገልጸው፣ ኢየሱስ ገንዘብ ለዋጮችንና ትልልቅ እንስሳትን የሚሸጡትን በታላቅ ብርታትና ኃይል ከቤተ መቅደሱ አባረራቸው፤ ዋኖሶችንና ርግቦችን የሚሸጡት ግን ወፎቹን ከቤተ መቅደሱ እንዲያወጡ ማሳሰቢያ ብቻ ተሰጣቸው።
  • ኢየሱስ ቤተ መቅደሱን “የአባቴ ቤት” በማለት ይጠራዋል፤ ከራሱም ጋር ያለውን ዝምድና ይገልጻል።
  • አይሁድ፣ ኢየሱስ ሁሉንም የማባረር ሥልጣን እንዳለው የሚያሳይ ምልክት ሲጠይቁት፣ ቤተ መቅደሱን ቢያፈርሱት እርሱ በሦስት ቀን እንደገና እንደሚገነባው ይናገራል። ይህም ኢየሱስን ከገደሉት በሦስተኛው ቀን ከሙታን እንደሚነሣ የሚናገር ትንቢት ነው።
  • ኢየሱስ፣ እውነተኛው “ቤተ መቅደስ” የራሱ ሥጋ መሆኑንም በግልጽ ያስረዳል። የእግዚአብሔር ሙላት የሚያድርበት አዲሱ ቤተ መቅደስ እርሱ ነው።
  • እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ ስለሚያድር፣ ቤተ መቅደሱ ነፍሳችንንም እንደሚወክል ሊታወቅ ይችላል። እኛ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንሆናለን። ከኢየሱስ ተልእኮዎች አንዱ፣ ኃጢአትን ሁሉ ከነፍሳችን በቅንዓት ማባረር ነው።

ማሰላሰያ፦ የመጽሐፍ ቅዱሱን ታሪክ እንደገና አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ነጥቦች ላይ በጥልቀት በማሰብ ጸሎታዊ ማሰላሰላችሁን ጀምሩ፦

  • በዓሉ እየቀረበ መምጣቱን ያሰላስሉ። ከበዓሉ በፊት ያሉትን ወራትና ሳምንታት በሐሳብ ይሳሉ። የሚደረገውን ዕቅድና የሚጠበቀውን ነገር ያስቡ። ይህ ክስተት ከመፈጸሙ በፊት ባሉት ወራት፣ ከጉዳዩ ጋር የተያያዙትን ሁሉ ያስቡ፦ ገንዘብ ለዋጮችን፣ ሻጮችን፣ ሀብታሞችን፣ ድሆችን፣ ተጓዦችን ሁሉ፣ እንዲሁም ኢየሱስንና ደቀ መዛሙርቱን።
  • በሰዎች እጅግ በተጨናነቀው የቤተ መቅደሱ አካባቢ ያለውን ሁከት፣ የእንስሳትን ሽታ፣ ጩኸቱን፣ ስግብግብነቱን፣ በቤተ መቅደሱ ያለውን የእንስሳት ደም፣ ደረቁን ሙቀትና የመሳሰሉትን በሐሳብ ይሳሉ።
  • ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደሱ ሲደርስ በሐሳብ ይሳሉ። የአባቱ ቤት ሲረክስ በማየቱ በውስጡ የሚነሣውን ጽድቅ የተሞላ ቁጣ ያሰላስሉ።
  • ከገመድ የተሠራውን ጅራፍ፣ ኢየሱስ እንስሳቱን ሲያባርር፣ ጠረጴዛዎቹን ሲገለብጥና የመሳሰሉትን ያሰላስሉ።
  • አሁን ወደ ነፍስዎ ቤተ መቅደስ ይመለሱ። እርሱም የአብ ቤት ነው። እርስዎ የእግዚአብሔር ቅዱስ ማደሪያ ናቸው።
  • ወደ ነፍስዎ እንዲገቡ የፈቀዱላቸውን ኃጢአትና ርኩሰትም ይመልከቱ። ይህን ሲያደርጉ፣ ኢየሱስ ይህን ኃጢአት ሲያይና በታላቅ ቅንዓት ሊያባርረው ሲፈልግ ይመልከቱት። የእርስዎ ምላሽ ምንድን ነው? ምስጋና ነውን? ወይስ ይቃወማሉ?

ዋና ምስል፦ክርስቶስ ቤተ መቅደሱን ሲያነጻ፣ በኤል ግሬኮ የተሳለ

የመደበኛው ዘመን ማሰላሰያዎች መግቢያ

  1. የጌታ ጥምቀት
  2. ሁለት ሰንደቅ ዓላማዎች
  3. ሦስት የሰዎች ወገኖች
  4. ፈተና
  5. የሐዋርያት መጠራት
  6. የቃና ሠርግ
  7. ቤተ መቅደሱን ማንጻት
  8. የተራራው ስብከት
  9. ማዕበሉን ማስታገስ
  10. በውኃ ላይ መራመድ
  11. ሐዋርያት እንዲሰብኩ ተላኩ
  12. የመግደላዊት ማርያም ወደ እግዚአብሔር መመለስ
  13. ክርስቶስ አምስት ሺህ ሰዎችን እንዴት እንደመገበ
  14. የክርስቶስ መለወጠ መልክ
  15. የአልዓዛር ከሙታን መነሣት
  16. በቢታንያ የተደረገው እራት
  17. ሦስት የትሕትና መንገዶች

ማውጫ