አማርኛ

የመግደላዊት ማርያም ወደ እግዚአብሔር መመለስ

የቅዱስ ሰዓት አምልኮ አቀራረብ

የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሉቃስ 7:36–50

የታሪኩ ዐውድ፦ ፈሪሳዊው ስምዖን ኢየሱስን በቤቱ እራት እንዲበላ ጋበዘው። እንግዶች ሲደርሱ በመሳም መቀበል፣ ራሳቸውን በዘይት መቀባትና እግራቸውን የሚታጠቡበት ውኃ መስጠት የተለመደ የእንግዳ አቀባበል ሥርዓት ነበር። ስምዖን ግን ከእነዚህ አንዱንም አላደረገም።

ይሁን እንጂ ይህ ታሪክ ስምዖን በእንግዳ አቀባበሉ ስላሳየው ጉድለት ከማማረር ይልቅ፣ ንስሐ የገባችውን የዚህችን ሴት ከልብ የመነጨ በጎነት ያሳያል። ኢየሱስ “እጅግ ስለወደደች” ይቅር እንደተባለች ይገልጻል። ስለዚህ የታሪኩ ዋና ትኩረት የእርሷ ፍቅርና ኢየሱስ በምሕረቱ የሰጣት ይቅርታ ናቸው።

ይህ ታሪክ ስምዖን በሌሎች ላይ በጣም ፈራጅ መሆኑንም ያሳያል። ኢየሱስ ሐሳቡን ዐውቆ፣ ፍቅር ስለጎደለው በእርጋታ ይገሥጸዋል፤ ሴቲቱን ግን በጥልቅ ፍቅሯ ምክንያት ያከብራታል።

ማሰላሰል፦ ከላይ የተጠቀሰውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በጸሎት መንፈስ ያንብቡ፤ ለማሰላሰልዎ የሚጠቅሙ ከሆነም በእነዚህ የማሰላሰያ ነጥቦች ይጠቀሙ፦

  • ኢየሱስ ወደ ስምዖን ቤት ሲደርስ በሐሳብዎ ይሳሉ። በእንግዳ አቀባበሉ ያለውን ጉድለት ያስተውሉ። ስምዖንን በሐሳብዎ ለመሳል ይሞክሩ።
  • የዚህችን ኃጢአተኛ ሴት ድፍረት ያሰላስሉ። ያለ ግብዣ ወደ ግብዣው በመምጣቷ ምን ያህል ተጨንቃ ሊሆን እንደሚችል ያስቡ። ማሸነፍ የነበረባትን ፍርሃቶች ያስተውሉ።
  • ዓይኖቿ ለመጀመሪያ ጊዜ ከኢየሱስ ዓይኖች ጋር ሲገናኙ፣ በልቧ ያለውን ለማየት ይሞክሩ። ወደ መሬት እንድትጎነበስ፣ እግሮቹን እንድትስም፣ በሽቶዋ እንድትቀባውና ራሷን መቆጣጠር እስኪሳናት ድረስ እንድታለቅስ ያደረጓትን ውስጣዊ ስሜቶች በሐሳብዎ ይሳሉ።
  • ወደ ኢየሱስ ልብ ይመልከቱ። ለእርሷ ያለውን ርኅራኄና ከልብ የመነጨ እንክብካቤ ይመልከቱ።

“ኃጢአቶችሽ ይቅር ተብለዋል።” እና “እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ።” የሚሉትን ቃላት ያሰላስሉ።

ዋና ምስል፦ ሩበንስ—የፈሪሳዊው ስምዖን ግብዣ

የመደበኛው ዘመን ማሰላሰያዎች መግቢያ

  1. የጌታ ጥምቀት
  2. ሁለት ሰንደቅ ዓላማዎች
  3. ሦስት የሰዎች ወገኖች
  4. ፈተና
  5. የሐዋርያት መጠራት
  6. የቃና ሠርግ
  7. ቤተ መቅደሱን ማንጻት
  8. የተራራው ስብከት
  9. ማዕበሉን ማስታገስ
  10. በውኃ ላይ መራመድ
  11. ሐዋርያት እንዲሰብኩ ተላኩ
  12. የመግደላዊት ማርያም ወደ እግዚአብሔር መመለስ
  13. ክርስቶስ አምስት ሺህ ሰዎችን እንዴት እንደመገበ
  14. የክርስቶስ መለወጠ መልክ
  15. የአልዓዛር ከሙታን መነሣት
  16. በቢታንያ የተደረገው እራት
  17. ሦስት የትሕትና መንገዶች

ማውጫ