አማርኛ

የመልአኩ ብሥራት ጸሎት

መሪ – የጌታ መልአክ ለማርያም አበሠራት።

ምላሽ – እርሷም በመንፈስ ቅዱስ ፀነሰች።

(ሰላም ላንቺ ማርያም….)

መሪ – እነሆ፣ እኔ የጌታ አገልጋይ ነኝ።

ምላሽ – እንደ ቃልህ ይሁንልኝ።

(ሰላም ላንቺ ማርያም….)

መሪ – ቃልም ሥጋ ሆነ።

ምላሽ – በመካከላችንም አደረ።

(ሰላም ላንቺ ማርያም….)

መሪ – ቅድስት የእግዚአብሔር እናት ሆይ፣ ጸልዪልን።

ምላሽ – ለክርስቶስ ተስፋ ቃሎች ብቁ እንድንሆን።

 
እንጸልይ፦
ጌታ ሆይ፣ ጸጋህን በልባችን እንድታፈስስ እንለምንሃለን፤
ይኸውም የልጅህ የክርስቶስ ሰው መሆን፣
በመልአክ መልእክት የተገለጠልን እኛ፣
በሕማሙና በመስቀሉ፣
ወደ ትንሣኤው ክብር እንድንደርስ ነው፤
በዚያው በጌታችን በክርስቶስ በኩል። 

አሜን።


ተጨማሪ ጸሎቶች

ዕለታዊ ማሰላሰያዎች