አማርኛ

የትንሣኤ ዘመን ማሰላሰያዎች

ለፋሲካ ዘመን ማሰላሰያዎች መግቢያ

  1. የኢየሱስ ትንሣኤ እና የመጀመሪያው መታየት
  2. ሁለተኛው መታየት
  3. ሦስተኛው መታየት
  4. አራተኛው መታየት
  5. አምስተኛው መታየት
  6. ስድስተኛው መታየት
  7. ሰባተኛው መታየት
  8. ስምንተኛው መታየት
  9. ዘጠነኛው መታየት
  10. ተጨማሪ መታየቶች
  11. የኢየሱስ ዕርገት
  12. መለኮታዊ ፍቅርን ለማግኘት የሚደረግ ተመስጦ

ዋና ምስል፦ ሉካ ጆርዳኖ – ትንሣኤ

ማውጫ

በለስላሳ ሽፋን በታተመ መጽሐፍና በኤሌክትሮኒክ መጽሐፍ መልክ ይገኛል፦

አማዞን – ጉግል ፕሌይ– አይቲዩንስ – ባርንስ & ኖብል


መግቢያ

አሥራ አንድ ማሰላሰያዎችን በያዘው በዚህ ክፍል፣ ክርስቶስ ከትንሣኤው በኋላ በተለያዩ ጊዜያት በመታየቱና ወደ ሰማይ በማረጉ ላይ ትኩረት ታደርጋለህ። በዚህ ክፍል ያሉት ማሰላሰያዎችና ልምምዶች የተመሠረቱት ቅዱስ ኢግናጥዮስ ባዘጋጀው መንፈሳዊ ልምምዶች ውስጥ በሚገኘው «አራተኛ ሳምንት» ላይ ነው። እነዚህ ማሰላሰያዎችና ልምምዶች በፋሲካ መጀመርና የጰንጠቆስጤ ታላቅ በዓል እስከሚከበርበት እስከ ፋሲካ ዘመን መጨረሻ ድረስ መቀጠል አለባቸው።

በዚህ ክፍል ያሉት ማሰላሰያዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ንባቡን አውድ ለማስረዳት መግቢያ ይሰጣሉ። ከዚያም በዝግታ፣ በጥንቃቄና በጸሎት እንድታሰላስልባቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ይቀርቡልሃል። በዚህ ወቅት፣ የኢግናጥዮስን የማሰላሰልና የተመስጦ ዘዴዎች አስቀድመህ በደንብ ተለማምደሃል በሚል ተስፋ፣ በነጥብ የተዘረዘሩ ሐሳቦች አልተሰጡም። ስለዚህ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባቡን አውድ ካነበብህ በኋላ፣ ለማሰላሰልህ መጽሐፍ ቅዱሱን ብቻ ለመጠቀም ሞክር፤ ራስህን በዚያ አውድ ውስጥ አስገባ፣ እያንዳንዱን መስመር እያጣጣምክ አንብብ፣ መንፈስ ቅዱስም እንደ ፈቃዱ እንዲናገርህ ፍቀድለት።