አማርኛ

የአድቬንት «ሆይ» አንቲፎናዎች

«ሆይ» የሚሉት አንቲፎናዎች ለገና በዓል ለመዘጋጀት ከዲሴምበር 17–23 ለ7 ቀናት ይጸለያሉ። የሰዓታትን አምልኮ ለሚያውቁ፣ እነዚህ በየቀኑ ከማርያም የምስጋና መዝሙር ጋር የሚጠቀሙባቸው አንቲፎናዎች ናቸው። መሠረታቸው የኢሳይያስ ትንቢቶች ሲሆኑ፣ ለመሲሑ የተሰጡትን ልዩ ልዩ መጠሪያዎች ይገልጣሉ።

ኦ ሳፒየንቲያ (ጥበብ ሆይ) ኢሳይያስ 11:2–3; 28:29
ኦ አዶናይ (ጌታ ሆይ) ኢሳይያስ 11:4–5; 33:22
ኦ ራዲክስ ዬሴ (የእሴይ ሥር ሆይ) ኢሳይያስ 1:1; 11:10
ኦ ክላቪስ ዳቪድ (የዳዊት ቁልፍ ሆይ) ኢሳይያስ 9:6; 22:22
ኦ ኦሪየንስ (የምትወጣ ፀሐይ ሆይ) ኢሳይያስ 9:1
ኦ ሬክስ ጀንቲዩም (የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ) ኢሳይያስ 9:5; 2:4
ኦ አማኑኤል (እግዚአብሔር ከእኛ ጋር) ኢሳይያስ 7:14

እያንዳንዱ አንቲፎና አጭር ስለሆነ፣ የገና በዓል ሲቃረብ መንፈሳዊ ዝግጅት ለማድረግ፣ በየቀኑ ጊዜ ወስዶ ማንበብ፣ በትርጉሙ ላይ ማሰላሰልና ቀኑን ሙሉ በተመስጦ መጸለይ ይጠቅማል።

ዲሴምበር 17

ፍጥረትን በኃይልና በፍቅር የምትመራ፣
የልዑሉ አምላካችን ጥበብ ሆይ፣
የእውቀትን መንገድ ልታስተምረን ና!

+++

ዲሴምበር 18

በሲና ለሙሴ ሕግን የሰጠህ፣
የእስራኤል ቤተሰብ መሪ ሆይ፣
በታላቅ ኃይልህ ልታድነን ና!

+++

ዲሴምበር 19

የእሴይ ግንድ ሥር፣
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ሁሉ ያለው ፍቅር ምልክት ሆይ፣
ሳትዘገይ ልታድነን ና!

+++

ዲሴምበር 20

የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ መንግሥት በሮች የምትከፍት፣
የዳዊት ቁልፍ ሆይ፣
ና፣ የጨለማ እስረኞችንም ነጻ አውጣ!

+++

ዲሴምበር 21

ብሩህ ጎሕ ሆይ፣
የዘላለማዊ ብርሃን ግርማ፣ የፍትሕ ፀሐይ፣
ና፣ በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ
በሚኖሩት ላይ አብራ።

+++

ዲሴምበር 22

የአሕዛብ ሁሉ ንጉሥና የቤተ ክርስቲያን የማዕዘን ድንጋይ ሆይ፣
ና፣ ከአፈር የሠራኸውን ሰው አድን!

+++

ዲሴምበር 23

አማኑኤል ሆይ፣ ንጉሣችንና ሕግ ሰጪያችን፣
ጌታ አምላካችን ሆይ፣ ልታድነን ና!

+++


ለአድቬንት ዘመን ተጨማሪ ይዘቶች