አማርኛ

ምሕረትንና የኃጢአት ይቅርታን መማጸን

ከመዝሙር 51

 ፍቅርና ቸርነት የተሞላህ እግዚአብሔር ሆይ፣ ምሕረት አድርግ።
ራራልኝ፣ የኃጢአቴንም አስከፊ እድፍ አስወግድልኝ።
እባክህ፣ እጠበኝ፤ ከዚህ በደል አንጻኝ። እንደገና ንጹሕ አድርገኝ።
አሳፋሪ ድርጊቴን እቀበላለሁና፤ ቀንና ሌሊት ያስጨንቀኛል።

ይህ በአንተና ወሰን በሌለው ምሕረትህ ላይ የተፈጸመ ኃጢአት ነው።

 እግዚአብሔር ሆይ፣ አዲስና ንጹሕ ልብ በውስጤ ፍጠር።
አንጻኝ፣ እንደ በረዶም ነጭ አድርገኝ።
ሐሳቦቼንና ምኞቶቼን አንጻ።

የድኅነትህን ደስታ እንደገና መልስልኝ፣ አንተንም ለመታዘዝ ፈቃደኛ አድርገኝ።

ኢየሱስ ሆይ፣ ማረኝ።
ኢየሱስ ሆይ፣ ማረኝ።

ኢየሱስ ሆይ፣ ማረኝ።

ኢየሱስ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ።
ኢየሱስ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ።

ኢየሱስ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ።

አሜን።

አሁን ይህን ክብር የተሞላ የዕርቅ ምሥጢር አትፍራ!