እኔ ብርታትህ ነኝ፣
ከሚያሰጋህ ነገር እጠብቅሃለሁና።
ጥበቃዬ ይሸፍንህ፤
ተቃዋሚዎችህንና ጠላቶችህን ስትጋፈጥም ድፍረትና ዕረፍት ይስጥህ።
ፍርሃትህ በልብህ ውስጥ ዋና ስፍራ አይያዝ፣
በአንተ በኩል ዕቅዴን አይፈጽምምና።
እንግዲህ ደፋር ብቻ ሁን፣
እኔ ከጎንህ ነኝና።
እኔ ብርታትህ ነኝ፣
ሥራዬን ለማከናወን ስትወጣ።
ለምን ትፈራለህ፣
እኔ የምለው እውነት ከሆነ?
በዚህ ጥያቄ መጽናናትን አግኝ፣
ይህ እውነትና ለአንተ የሰጠሁት ተስፋ ቃል ነውና!
መንገድህ አይዛነፍ፣
እኔ ከወሰንኩልህ አቅጣጫ።
እርምጃዎችህ አይመሩህምና፣
ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ።
