ለምትሻው ሁሉ ወደ እኔ ና።
ባለው ሁሉ እኔን ፈልገኝ።
አሁን ባለው ሁሉ እኔን እየኝ።
ወደፊት በሚመጣው ሁሉ መገኘቴን ተጠባበቅ።
መገኘቴን ትፈራለህ?
ከእኔ ትሸሻለህ?
ከመንፈሴ ጋር መገናኘትን ታስወግዳለህ?
የመሸሽ ልማድህን ወደ ጎን ተውና
በፊቴ ለመሆን ና።
እጄን እይ፤ እንዴት እንደምትቀበልህና መንገድህን እንደምትመራም ተመልከት።
በአመራሯ ታመን፤ ለአንተ ለምትሰጣቸውም መመሪያዎች ተገዛ።
ምልክቶችንና ተምሳሌቶችን ትጠባበቃለህ?
እነዚህን ለማየት ያለመቻልህ ዕውርነት ጥርጣሬ ይፈጥርብሃል?
አድምጥ፤ እኔንም ስማኝ።
ተመልከት፤ ለአንተ የምሰጠውንም አመራር እይ።
ታመን፤ ከአንተ ጋር እንዳለሁም ዕወቅ።
ይህ እውነት ከሆነ፣
እንግዲያው ምን ጥያቄ፣ ጥርጣሬ ወይም ፍርሃት
ከአንተ ጋር ሊቀር ይገባል?
ይህ እውነት ከሆነ፣
እንግዲያው የትኛውን መንገድ ትከተላለህ?
