አማርኛ

እምነት

እምነትን የሚጠይቁ ብዙ አጋጣሚዎች ይሰጡሃል።
እነዚህ ፈተናዎች የሚሰጡህ እንድታድግ ነው።
ሁልጊዜ ያለውን መልካም ነገር ፈልግ፣
በእነዚህ ተሞክሮዎች ውስጥ።

እንድትሳሳት አትፍቀድ፣
ደስ የማያሰኙ በሚመስሉህ ነገሮች፣
በዓይንህ በምታያቸው።
ከእነዚህ ውጫዊ ገጽታዎች አልፈህ ተመልከት፤
ላንተ የሰጠሁትን ስጦታ
እውነተኛ ትርጉም ተመልከት።
ጠቢብ ሰው ይህን በቀላሉ ያያል፣
እውቀት ለሌለው ግን ግልጽ አይደለም።

ጥርጣሬ ሲገባህ እኔን አዳምጥ፤
እውነቱን እንድታይ እረዳሃለሁ፣
በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ።

በእኔ ለመታመን አትፍራ፣
ወደ ተወሰነልህ ስፍራ እመራሃለሁና፣
ለአንተ ወደ መረጥሁት።

በሌሎች ውስጥ እውነትን ፈልግ፣
ለእኔም ታማኝ የሆኑትን እመን።
እነዚህ ሰዎች ተሰጥኦ ያላቸው ናቸው፣
ከፈቀድህላቸውም ይረዱሃል።

ቀጣዩ መንፈሳዊ ማሰላሰያ

ማውጫ