እምነት ለአንተ የሰጠሁት ስጦታዬ ነው፤
በተስፋና በእምነት ይሙላህ።
ኃይሉንም ሆነ ውጤቱን አትጠራጠር፤
በጸጋ ይሙላህ።
መጨነቅም ሆነ መፍራት አያስፈልግህም፤
ልብህ በሰላም ይሞላ።
ያለዚህ ሰላም አንድም ቀን እንዲያልፍ አትፍቀድ።
ታዲያ አእምሮህን ምን ሊያሳስበው ይገባል፣
ይህ እምነት እንዲቀርጽህ ከፈቀድህለት?
ታዲያ ሊውጥህ የሚችለው ምንድን ነው?
ታዲያ ከብቦ የሚያስፈራራህ ምንድን ነው?
ይህ እምነት በውስጥህ እንዲኖር ጠይቅ፣
ሰላሜም በውስጥህ ይኖራል።
ይህን ገጽ ያጋሩ፦
