አማርኛ

ፍርሃት ቦታ የለውም

ስለ እኔ ብዙ ተሠቃይተሃል።
ታዲያ የትኛው መጽናናት ሊያበረታህ ይችላል?
ታዲያ የትኞቹ ቃላት ሐዘንህን ያስታግሳሉ?
የትኛው ኃይል ይጠብቅሃል?

ስለ እነዚህ ጥያቄዎች አትጨነቅ፤
የሚያስፈልግህ ሁሉ በሚያስፈልግህ ጊዜ ይሰጥሃልና።

በመንገዶቼና በአሠራሬ ታመን፤
ዕቅዴ እየተፈጸመ ሲሄድ፣
ዓላማዬ ይገለጥልሃልና።

ሐሳብህን አታስጨንቅ፣
ስለ ዓላማዎቼ በመፍራት፤
የሚያስፈልገው ሁሉ በመንገዶቼ መታመን ብቻ ነውና።

ፍርሃትህ ዓላማዎቼን ሊረዳ አይችልም፤
ፍርሃት የዕቅዴ አካል አይደለምና።

ታዲያ ሥራዎቼን በአዲስ እይታ ተመልከት፤
ሰላምና እርካታ ይሰጡሃልና።

ቀጣዩ መንፈሳዊ ማሰላሰያ

ማውጫ