አማርኛ

ዕለታዊ ጸሎቶች

ከሳምንታዊው የቅዱስ ሰዓት ጸሎት በተጨማሪ፣ አንድም ቀን ሳታቋርጥ በየቀኑ ለጸሎትና ለማሰላሰል ራስህን መስጠት አስፈላጊ ነው። እንዲሁም ማሰላሰሎቹና የሚያፈሩት መልካም መንፈሳዊ ፍሬ ከሳምንት ወደ ሳምንት አንዱ በሌላው ላይ እየተገነባ እንዲያድግ መፍቀድ አስፈላጊ ነው። እግዚአብሔር ወደ ጸጋው ሕይወት ይበልጥ እየጠለቅህ በምትገባበት ጉዞ ሊመራህ ይፈልጋል። የሚከተሉት ዕለታዊ ጸሎቶች እርሱ ወደሚመራህ አቅጣጫ ወደፊት እየተራመድህ በዚያ ጉዞ እንድትቀጥል ይረዱሃል።

እግዚአብሔር እንዲመራህ ለመፍቀድ የሚረዳ ሌላ መንገድ፣ በጸሎትህ ያገኘኸውን መንፈሳዊ ግንዛቤ በአጭሩ የምትጽፍበት ማስታወሻ መያዝ ነው። ማስታወሻዎችን በመያዝና አዘውትረህ መልሰህ በማንበብ፣ ለልብህ ከሚናገረው ከእግዚአብሔር ድምፅ የተነሣ የተገለጡልህን አሳሳቢ ጉዳዮች ለመፍታት፣ ኃጢአቶችን ለማሸነፍና በተገኙት ድሎች ለመደሰት ትችላለህ። እነዚያን ማስታወሻዎች በየማታው በሌሊት ጸሎትህ ጊዜ ትጠቀምባቸዋለህ። ከመረጥህ፣ ከመጻፍ ይልቅ በአእምሮህ ብቻ በመያዝ ይህን ማድረግ ትችላለህ።

የጠዋት ጸሎት

የከሰዓት በኋላ ጸሎቶች

የሌሊት ጸሎት ከዕለታዊ የሕሊና ምርመራ ጋር