
ምን ያህል ሆምጣጤ ሰጠሁህ፣
ጮኸህ ለገለጽከው ጥምህ ማርኪያ፣
አንተም በሥቃይ ለመቅመስ ብቻ የቀመስከውን፣
ምሬቱ ጥምህን ሊያረካ ስላልቻለ?
ሆኖም ጥልቅ፣ መለኮታዊና ፍጹም ፍትሐዊ በሆነ ምሕረትህ፣
ይህንንም እንኳ በታላቅ ትሕትና ተቀበልክ፣
ይህን አዳም እስከ አፈሩ ድረስ እየወደድክ፣
ላብህ በፈሰሰበት በዚያ የአትክልት ቦታ መሬት ላይ።
ከአንድ ሰዓት የበለጠ አልጠየቅኸኝም፣
በዚያ በሐዘንና በጭንቀት በተሞላብህ ሌሊት።
እኔ ግን ዐይኖቼ በእንቅልፍ ከብደው፣ ልቤም ደክሞ፣
በግዴለሽነት ብርድ ውስጥ ተኛሁ።
እንደገና ግን የእናትህን እጅ ይዤ እቆማለሁ፣
በመጀመሪያ የነበረኝንም ፍቅር እለምንሃለሁ፣
በእርሷ አማካይነት እንድረዳ ተስፋ እያደረግሁ፣
የልብህን ቁስልና “ተጠማሁ” የሚለውን ጩኸትህን።
-አባ ቲሞቲ ጄ. ድሬፐር
