አማርኛ

ክርስቶስ፣ የተስፋ ሻማ

አፍቃሪ አባታችን እግዚአብሔር ሆይ፣ ወልድህን፣

ኢየሱስ ክርስቶስን፣ ወደዚህ ዓለም የላክኸው፣

ሁሉንም የክፋት ኃይሎች፦ ኃጢአትን፣ ሥቃይንና ሞትን ለመቋቋም፣

ክፋትንም በበጎነት ኃይል ለማሸነፍ፣

ጥላቻንም በፍቅር ኃይል፣

በኢየሱስ ለእኛ ባለህ ታላቅ ፍቅር ለማሸነፍ ነው።

 

ጨለማን ፈጽሞ እንዳንረግም እርዳን፤

ይልቁንም ከአንተ ጋር በመሆን

ብርሃንህን ወደዚህ ዓለም እንድናመጣ እርዳን፤

ይህ ብርሃን ወልድህ ነው፣

በቤተ ልሔም ከድንግል ማርያም የተወለደው።

የብርሃንህ

እና የፍቅርህ መሣሪያዎች እንድንሆን፣ አንድ ልዩ የደግነት ሥራ በመሥራት

ወይም ልዩ የአንተ መሣሪያ በመሆን

በዚህ አዲስ ዓመት እርቅን እንድናሰፍን እርዳን።

 

የምንለኩሰው የክርስቶስ ሻማ፣

በጨለማ ወደተዋጠ ዓለም ብርሃንን፣

ተስፋ ወደቆረጠ ዓለምም ተስፋን ለማምጣት ያለንን ምኞት የሚያመለክት ይሁን።

ይህንንም በጌታችን በክርስቶስ እንለምናለን።

አሜን።


ተጨማሪ ጸሎቶች

ዕለታዊ ማሰላሰያዎች