በእኔ ላይ አተኩር።
ትኩረትህን የሚበትነውን አስወግድ።
ፍቅሬ እንዲከብብህ ፍቀድ።
መገኘቴን አትፍራ፣
የዋህ ነኝና፣ በደግነትም እንከባከብሃለሁ።
ልብህን ወደ እኔ አንሣ፣
እኔን የምታውቅበት መንገድ ይህ ነውና።
ጸጋዬ ወደ ልብህ ዘልቆ ይግባ፣
በፈዋሽ ዳሰሳውም ይሙላህ።
ራስህን ለእኔ ከመስጠት አታመንታ፣ ወደ ኋላም አትበል፣
የእኔ እንድትሆን እፈልጋለሁና።
ራስህን ነፃ አድርግ፣ መንፈስህንም ከጸጋዬ ጋር አንድ አድርግ።
ይህን ገጽ ያጋሩ፦
