
ሃሌ ሉያ! ጌታ ኢየሱስ ሆይ፣ ከሙታን ተነሥተሃል፤ በክብርም ድል ነሥተሃል!
ጌታ ሆይ፣ በትንሣኤህ በዓል ላይ እንድሳተፍ ስላደረግኸኝ ከልቤ የመነጨ ምስጋና አቀርብልሃለሁ! በአንተ ድል በተገኘው አዲስ ሕይወት እንድካፈል እስክትጋብዘኝ ድረስ እጅግ ስለወደድኸኝ አመሰግንሃለሁ።
ውድ ጌታ ሆይ፣ ወደ ትንሣኤ የሚወስደው መንገድ እጅግ ከባድ ሥቃይና መከራ የተሞላበት ነበር። ሕይወትህን ሙሉ በሙሉ መሥዋዕት አድርገህ እንድታቀርብ ጠየቀብህ። ምንም ሳታስቀር፣ እስከ መጨረሻው የደም ጠብታ ድረስ ሕይወትህን አፈሰስህ።
ከሙታን የተነሣህ ጌታ ሆይ፣ አስደሳቹ መልእክት መከራና ሞት መጨረሻ አለመሆናቸው ነው። በአዲስና በተከበረ ሥጋ በድል ተነሣህ፤ በአንተ የሚያምኑ ሁሉ እንዲሁ እንዲነሡም በሩን ከፈትህ። ውድ ጌታ ሆይ፣ በትንሣኤህ ክብርም እንድካፈል፣ ወደ መከራህና ሞትህ ሳበኝ። ያን ሁሉ መከራ ስትታገሥ የነበረህን ድፍረት ስጠኝ። በሕይወቴ ያሉትን መስቀሎች በአንተ ኃይል እንድጋፈጥ እርዳኝ። ይህን ሳደርግ፣ ከአንተ ጋር ከተዋሐዱት መከራዎች ሁሉ የምታስገኘውን አዲስ ሕይወት እየጠበቅሁ፣ በተስፋ ሙላኝ።
ሃሌ ሉያ! ጌታ ኢየሱስ ሆይ፣ ከሙታን ተነሥተሃል፤ በክብርም ድል ነሥተሃል!
ሃሌ ሉያ! ውድ ጌታ ሆይ፣ ስለ ትንሣኤህ ክብርና ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን!
ሃሌ ሉያ! የትንሣኤህ ክብር እስከ ዘመን ፍጻሜና ለዘላለም የተወደደ፣ በልብ የተቀበሉትና የታወጀ ይሁን!