
እጅግ ውድ ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ፣ በዚህ ሌሊት የመጨረሻውን ራትህን ከሐዋርያትህ ጋር ለመካፈል ተሰበሰብህ። ይህ ግን ተራ ምግብ አልነበረም። ይህ ዓለምን ለማዳን በቅርቡ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው እጅግ ቅዱስ ሥጋህና የሚፈሰው እጅግ ቅዱስ ደምህ ስጦታ ነበር።
ውድ ጌታ ሆይ፣ ይህን ሌሊት ከአንተ ጋር በጸሎትና በማሰላሰል እንዳሳልፍ ፍቀድልኝ። ከራት በኋላ፣ ለመያዝህ እየተዘጋጀህ፣ ሐዋርያትህ ለአንድ ሰዓት ከአንተ ጋር እንዲቆዩና ነቅተው እንዲጠብቁ ጋበዝሃቸው። ሐዋርያት ግን ተኙ፤ በመራራ ሥቃይህም ብቻህን ተዉህ።
ውድ ጌታ ሆይ፣ በዚህ ሌሊት ከአንተ ጋር በንቃት እንድቆይ በፍቅር ያቀረብኸውን ለስላሳ ግብዣ እቀበላለሁ። ስለ ኃጢአቴ ልትታገሠው የነበረውን ስደት ለመጋፈጥ ወደ ተዘጋጀው ልብህ እንድገባ አድርገኝ። ቅዱስ ልብህን እንዳጽናናና ከእርሱ የፈሰሰውን ፍቅርና ምሕረት እንዳውቅ አድርገኝ።
ጌታ ሆይ፣ በሕይወቴ ያሉትን መስቀሎች ስጋፈጥ፣ ለአብ ፈቃድ «እሺ» እንድል መለኮታዊ ድፍረትህንና ብርታትህን ስጠኝ። ለእኔ ያለህ ፍቅር የተትረፈረፈና በሁሉም ረገድ ፍጹም ነው። ያንን ፍቅር እንዳውቅ፣ እንድቀበለውና ወደ ሕይወቴ እንዲገባ እንድፈቅድለት እርዳኝ።
ውድ ጌታ ሆይ፣ በዚህ ሌሊት ከአንተ ጋር ነቅቼ እጠብቃለሁ። እወድሃለሁ፤ በሙሉ ልቤ እንድወድህ እርዳኝ። ኢየሱስ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ።
ለሳምንተ ሕማማት የተዘጋጁ ሁሉም ዕለታዊ ማሰላሰያዎች
ጸሎተ ሮዛሪዮ – የሐዘን ምሥጢራት (ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባቦች ጋር)
ግጥም – የከሰል እሳት
